በመርሐቤቴ ወረዳ እና በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር በአርበኞች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ።
በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ እና በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር አመራሮች መካከል የወዳጅነት እግር ኳስ ጨዋታ ግንቦት 30/2018ዓ.ም ተካሂዷል።
የወዳጅነት እግር ኳስ ጨዋታው በመርሐቤቴ ወረዳና በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት የተካሄደ ሲሆን ጨዋታው የሁለቱም መስተዳድር አመራሮች ይበልጥ አንድነት ለማጠናከር ታስቦ የተደረገ ነው ተብሏል።
ውጤቱም በመርሐቤቴ ወረዳ አመራሮች 2_0 በሆነ አሸናፊነት ዉድድሩ ተጠናቋል።


