ከወንጭት እስከ ጀማ ያለው የፌደራል መንገድ ጥገና ስራ መጀመሩ ተገለፀ
የመርሐቤቴ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት (ግንቦት 26/2018 ዓ/ም)
በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ ከወንጭት እስከ ጀማ ያለው የፌደራል መንገድ በፌደራል መንገዶች አስተዳደር(ERA) ጥገና ስራ ተጀምሯል።
የመንገድ ጥገና ፎርማን አቶ ደመቀ ሎኃ እንደገለፁት ከጃማ ደጎሎ እስከ ወንጭት ጥገናውን እንዳጠናቀቁ አንስተው፤ በወረዳው ከወንጭት እስከ ጀማ ያለውን የፌደራል መንገድ ጥገና ስራ በማከናወን ላይ ነን ያሉ ሲሆን እስከ ሰኔ 15 ድረስ የመንገድ ጥገናውን ለማጠናቀቅ አቅደው እየሰሩ እንደሆነና በጣም የተጎዱ መንገዶችን እየጠገንን እንገኛለን ሲሉ አንስተዋል።
የመርሐቤቴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታው በላይግዛው እንደገለፁት ከጃማ እስከ ወንጭት ያለው መንገድ መጠናቀቁን አንስተው፤ አሁን ላይ ከወንጭት እስከ ጀማ ያለው የፌዴራል መንገድ ጥገና እየተከናወነ እንደሆነና አሁን ላይ በመርሐቤቴ ወረዳ በአገሪት ቁምአምባ ቀበሌ ልዩ ስሙ መጋያጃ እየተባለ በሚጠራው ቦታ የጥገና ስራ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
የመንገድ ጥገና ስራውን የመርሐቤቴ ወረዳ አስተዳደር አመራሮች በቦታው በመገኘት ምልከታ አድርገዋል።



See less