አልማ በትምህርት ዘርፉ ላይ የተሻለ ስራ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።
በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ በአልማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተደረገ የበጀት ድጋፍ በኮሶ ጠረህና ቀበሌ ጥራቱን የጠበቀ አንደኛ ትምህርት ቤት ተገንብቶ ተመረቀ።
ከአሁን በፊት በቀበሌው ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ተቋም አለመኖሩ የተገለፀ ሲሆን አልማ ባስገነባው የመማሪያ ክፍሎች ማህበረሰቡ ደስተኛ መሆናቸው ተገልጿል።
የወረዳው አልማ ጽህፈት ቤት ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ቀበሌዎች ልዮ ልዩ የትምህርት እና የጤና ተቋማትን እያሰገነባ እንሚገኝም ተጠቅሷል።


See less