አማራ ልማት ማህበር (ALMA) የአማራ ህዝብ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ትምህርታዊ እድገትን ለማጎልበት የተቋቋመ የልማት ማህበር ነው። ማህበሩ በ1984 ዓ.ም. ተመስርቶ በተለያዩ የልማት መስኮች ላይ በመስራት የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል አስተዋፅኦ ሲያደርግ ቆይቷል።
ማህበሩ በዋናነት በትምህርት፣ በጤና፣ በውሃና ንፅህና፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በሴቶችና ወጣቶች አቅም ግንባታ፣ በሕፃናት ድጋፍ እና በተለያዩ የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራሞች ላይ ይሰራል።
በተጨማሪም በአደጋ ጊዜ ሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ እና ዘላቂ የልማት ፕሮጀክቶችን በመተግበር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል።
አማራ ልማት ማህበር ከመንግስት፣ ከማህበረሰብ እና ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ያከናውናል።
የአልማ ልማት ማህበር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ልማት ተግባር
በ2018 ዓ.ም የአልማ ልማት ማህበር በመርሐቤቴ ወረዳ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገቢ በማሰባሰብ በትምህርት ቤቶች የመማሪያ ክፍሎችና ሌሎች የትምህርት መሠረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል።